Timket Celebration (Epiphany) by Megabi Haddis

ጥምቀት ማለት ፤

መጠመቅ ፤ መነከር ፤መደፈቅ ፤ በውሃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው::

በምሥጢረ ጥምቀት ትምህርታችን:-
– የጥምቀት ምሳሌዎች ፤
– የጥምቀት አመሠራረት ፤
– በጥምቀት የሚገኝ ጥቅም ፤
– ለጥምቀት የተወሰነ ዕድሜ ፤ የሚሉትን እንማራለን ።

1 የጥምቀት ምሳሌዎች በብሉይ ኪዳን ዘመን የተፈጸሙና ለአማናዊው የሐዲስ ኪዳን ጥምቀት ምሳሌ ከነበሩት መካከል የሚከተሉትን እናያለን ።–የጥፋት ውሃ በኖኅ ዘመን በበደላቸው ተጸጽተው ንስሓ ያልገቡ ሰዎችንና (ከኖኅና ቤተሰቡ እንዲሁም ለዘር እንዲቀሩ ከተደረጉት ፍጥረታት በቀር) በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ያጠፋው ማየ አይኅ(የጥፋት ውሃ) የጥምቀት ምሳሌ ሲሆን ፤ ከጥፋት ውሃ የዳኑት ኖኅና ልጆቹ ፤ ከክርስቶስ ጎን ለጥምቀታችን በፈሰሰው ትኩስ ውሃ በጥምቀት ከእግዚአብሔር ተወልደው ከፍርድ ለሚድኑ ምዕመናን ምሳሌ ነው ። ዘፍ 7 ፥ 1 ። ዘፍ ፥ 19 ፡ 1 ። 1ዼጥ 3 ፥ 28 ።– ግዝረት ዘፍ 17 ፥ 14 ። ግዝረት ለጊዜው ለእስራኤል ዘሥጋ መለያ ሲሆን ፤ ፍጻሜው ግን ሊመጣ ላለውና ለእሥራኤል ዘነፍስ ምዕመናን መክበሪያ ለሆነው ለጥምቀት ምሳሌ ነው ። ቆላ 2 ፥ 14 ።– የኤርትራ ባህር (ቀይ ባህር)ዘፀ 14 ፥ 21 ። 1ቆሮ 10 ፥ 1 ። ሙ ሴ የክርስቶስ ፤ ባህሩን የከፈለባት በትር የመስቀል ፤ ባህረ ኤርትራ የፍርድና የሲኦል ፤ በተከፈለው ባህር የተሻገሩት እስራኤል በመስቀሉ

      ላይ በፈሰሰው ደሙ በጥምቀት ከእግዚአ ብሔር ተወልደው ባህረ ኃጢአትን የሚሻገሩ ምዕመናን ምሳሌ ነው ።– የዮርዳኖስ ባህር ኢያሱ 3 ፥14 ። ኢያ 4 ፥ 15 ። ኢያሱ የክርስቶስ ፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት ፤ ይርዳኖስን የተሻገሩ እስራ ኤል በክርስቶስ አምነው በመጠመቅ የዳኑ ምዕመናን ምሳሌ ነው ።– የዮሐንስ ጥምቀት ማቴ 3 ፥1 ። ዮሐንስ ህዝቡን የንስሓ ጥምቀት እያጠመቃቸው ከቆየ በኋላ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ ግን እነሆ የእግዚአብሔር በግ በማለት ወደ ጌታ መርቷቸዋል ስለዚህ የዮሐንስ ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ለአማናዊዉ የጌታ ጥምቀት

    የሚያዘጋጅ ነውየጥምቀት አመሰራረትጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን ሲሆን ፤ የተጠመቀበትም ምክንያት ።– በብሉይ ኪዳን ያልተገለጸ አንድነት ሶስትነቱን (ምሥጢረ ሥላሴን) ለመግለጽ ። ማቴ 16 ፥ 17 ።
– እንዴት በማንና የት መጠመቅ እንዳለብን ሊያስተምረን አብነት ሊሆነን ። ዮሐ 13 ፥ 12 ።
– ጠላት ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ ። ቆላ 2 ፥ 16 ።
አዳምና ሄዋን ዕፀ በለስን በልተው የአምላካቸውን ትእዛዝ በመተላለፋቸው የተወሰደብንን ልጅነት የምናስመስልበትንና ከእግዚአብሔር የምንወለድበትን አማናዊ ጥምቀት በዮሐንስ እጅ ተጠምቆ ከመሰረተልን በኋላ ፤ በጸሎተ ሐሙስ ማታ የሐዋርያትን እግር በማጠብ አሳይቷቸዋል። ምክንያቱም በዚያ ሰዓት ቅዱስ ዼጥሮስ እኔ አጥብሀለሁ እንጅ አንተ የእኔን እግር አታጥበኝም ብሎ በተከራከረበት ጊዜ ፤ ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር አንድነት የለህም ማለቱ ከእግዚአብሔር አንድ የምንሆንበት በመንፈስ የምንወለድበት ብቸኛው መንገድ

ጥምቀት መሆኑን እንረዳለን ።

ጌታችን ጥምቀትን ከመሠረተልን በኋላ እኛም ከውሃና ከመንፈስ በመወለድ ልጅነትን ተቀብለን መንግስቱን እንደምንወርስ ለኒቆዲሞስ ያስተማረውን እናስታውሳለን ። ዮሐ 3 ፥ 1።
ለሐዋርያትም ሥጢረ ጥምቀት በጸሎተ ሐሙስ ይፈጸምላቸው እንጅ መንፈስ ቅዱስ የወረደላቸው ጌታ በተነሳ በአምሳኛው ፤ ባረገ በአስረኛው ቀን ነው ። ከነሱ በኋላ ምዕመናን ሲጠመቁ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ሲወርድባቸው በግልጽ ይታይ ነበር ። የሐ ሥ  2 ፥ 1 ። የሐ ሥ 8 ፥ 14 ።

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው የተነገረውን ትንቢት የተመሰለውን ምሳሌ ለመፈጸም ነው ።

ምሳሌ

–አብርሐም የአሕዛብን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ ዮርዳኖስን መሻገሩ ፤የምዕመናን ጥምቀት መልከ ጼዴቅ የጌታ ምሳሌ ። ዘፍ 14 ፥ 17 ። ዕብ 6 ፥ 1 ።– እሥራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ርስታቸው ከነዓን መግባታቸው ፤ ምዕመናንአምነው ተጠምቀው ወደ ሰማያዊቷ ርስታቸው መንግስተ ሰማያት የመግባታቸው ምሳሌ ። ኢያ 3 ፥ 14 ።– ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ማረጉ ፤ ምዕመናን ተጠምቀው ዕርገተ ነፍስ የማግኘታቸው ምሳሌ ። 2ነገ 2 ፥ 8 ።

    – ንዕማን በዮርዳኖስ ተጠምቆ ከለምጽ መዳኑ ፤ ምዕመናን ተጠምቀው ከነፍስ ለምጽ የመዳናቸው ምሳሌ ። 2ነገ 5 ፥ 14 ።ትንቢትባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ ። መዝ 113 ፥ 3 ።በውሃ የተጠመቀበት ምክንያት

– ውሃ በየትም ቦታ ስለሚገኝ ፤ ሰዎች በቀላሉ ልጅነትን አግኝተው መንግስተ ሰማያት እንዲወርሱ ።
– ውሃ የደረቁ ዕፀዋትን እንደሚያለመልም ፤ ምዕመናን ተጠምቀው ልምላሜ ነፍስ እንዲያገኙ ።
– ውሃ ከእድፍ እንደሚያነጻ ፤ ምዕመናንም ተጠምቀው ከኃጢአት እንዲነጹ ። የሐ 2 ፥ 38 ። ህዝ 36 ፥ 25 ።
– ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋ ፤ ምዕመናንም ተጠምቀው ከገሃነመ እሳት እንዲድኑ ። ማቴ 3 ፥ 6-12 ።

በጥምቀት የሚገኝ ጥቅም

     – በምንጠመቅበት ጊዜ በመርገም ከተላለፈብን ኃጢአት ሥርየት እናገኛለን ። ህዝ 36 ፥ 25 ። የሐ 2 ፥ 38 ።
– በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ስንወለድ ፤ የተወሰደብን ልጅነታችን ይመለስልናል ዮሐ 3 ፥ 1 ።
– ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ። ከሚለው የገሃነመ እሳት ፍርድ እንድናለን ። ማር 16 ፥ 16 ።
– በውሃው ስንደፈቅ ከክርስቶስ ጋር የመሞታችን ፤ ከውሃ ስንወጣ የመነሳታችን ምሳሌ ። ሮሜ 6 ፥ 3 ።
– በጥምቀት ከጌታችን ጋር: ገላ 3 ፥ 27 ፤ ከምዕመናን ጋር አንድ እንሆናለን ። ቆላ 2 ፥ 11 ።

ለጥምቀት የተወሰነ ዕድሜ

በሐዋርያት ስብከት ያመኑና በማንኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሁሉ ይጠመቁ ነበር የሐ ሥራ 16 ፥ 15 ። 1ቆሮ 1 ፥ 15 ። በኋላ ግን ወላጆቻቸው ሊያስተ ምሯቸው ቃል እየገቡ ልጆቻቸውን ወንዶችን በአርባ ሴቶችን በሰማንያ ቀናቸው ማጥመቅ ተጀመረ ።

ለዚህም መሠረቱ

   – የእስራኤል ልጆች በተወለዱ ወንድ በአርባ ሴት በሰማንያ ቀናቸው ወላጆቻቸው መባዕ (ስጦታ) ይዘውላቸው ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ በእስራኤልነት (የዜግነት) መዝገብ እያስመዘገቡ የተስፋዋ ምድር ከነዓን ባለመብቶች (ወራሾች) ያደርጓቸው እንደነበረ ሁሉ ፤ ዛሬም ህጻናት ወላጆቻቸው ሃይማኖታቸውን ሊያስተምሯቸው ሃላፊነት ወስደው የክርስትና አባት ወይም እናት በተጨ ማሪ ቃል ገብተው ክርስትና በመነሳት (በመጠመቅ) የወላጆቻቸውን ርስት መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉ ።
ከአርባ እና ከሰማንያ ቀን በኋላ የሚመጡ ተጠማቂዎች ግን ሃይማኖታቸውን ተምረው ካመኑ በኋላ በማንኛውም የዕድሜ ክልል መጠ መቅ ይችላሉ ። በሕይወት እስካሉ ድረስ መቸም ቢሆን ከመጠመቅ የሚያግዳችው ነገር የለም ።

epiphany

         አንድ ተጠማቂ የሚያሟላቸው ነገሮች

ከመጠመቁ በፊት ተጠማቂው ሃይማኖቱን በሚገባ ተምሮ ማመንና መመስከር አለበት ። ተጠማቂው ህጻን ከሆነ ወላጆቹ ወይም የክርስታና አባት እናት ቀርበው ሊያስተምሩት ቃል መግባት አለባቸው ።በሚጠመቅበት ጊዜ በውሃ ውስጥ ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ማለት አለበት ፤ የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ምሳሌ ነውና ። ተጠማቂው የሚጠመቀው በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው ። ማቴ 28 ፥ 19 ። ተጠማቂዎች ባለትዳሮች ከሆኑና ቤተሰብም ካላቸው ሁሉም ተምረው አምነው በአንድነት መጠመቅ አለባቸው ።ከተጠመቀ በኋላ መቁረብ (ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል) ይገባል ። ይህ ካልሆነ ጥምቀቱ ህያው አይሆንም ። ቃሉ ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ይላልና። እያንዳንዱ ለእርሱ ሲል የተቆረሰውን ቅዱስ ሥጋና የፈሰሰውን ክቡር ደም ተቀብሎ ከበደሉ መንጻት አለበት። በጥምቀት የተቀበልነው ልጅነት የሚረጋገጠው ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል ብቻ ነውና ።

ጥምቀት አንዲት ናት ። ኤፌ 4፡

– ከወላጆቻችን በሥጋ የምንወለደው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ሁሉ ከውሃና ከመንፈስም ከእግዚአብሔር የምንወለደውም (የምንጠመቀው) አንድ ጊዜ ብቻ ነው ። በመሆኑም ጥምቀት አንዲት ናት አትደገምም ።
– የጥምቀት ምሳሌ የነበረው ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደነበረ ሁሉ ጥምቀትም አንድ ጊዜ ነው ። ቆላ 2 ፥ 11 ።
– ከጌታ ሥጋና ደም የምንሳተፍበት ምሥጢር በመሆኑ ጌታም የሞተውና የተነሳው አንድ ጊዜ ነውና አንድ ጊዜ ብቻ እንጠመ ቃለን ። ሮሜ 6 ፥ 3 ። በእኛ ቤተ ክርስቲያን ከተጠመቀ በኋላ በሌላ ሃይማኖት ገብቶ እንደገና ቢጠመቅ ወይም ከሌላ እምነት ተከታይ ጋር ጋብቻ ቢመሠርት በንስሓ ከተመለሰ በኋላ መጽሐፈ ቄድር ተጸልዮለት ይጠመቃል ። ይህ ግን ሁለተኛ ጥምቀት ሳይሆን የንስሓ ጥምቀት ይባላል ።
ከኦርቶዶክሳውያን ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት (Oriental Churches) በቀር በሌላ ማንኛውም ቤተ ክርስቲያን ከተጠመቀ በኋላ አምኖ የሚመጣ ሰው ቢኖር እንደገና ይጠመቃል ።