ዛፎች ለምን?By gyisma33 ዛፎች ለምን? አንድ ቦታ ሳነብ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት እንዳለቀ እ ኤ አ 1945 የኢትዮጵያ መልከዓ ምድር 42 % በደን የተሸፈነ ነበር። በአሁኑ ጊዜ የሚገመትው ~ 2% እንደሆነ ነው። ይህም በአብዛኛው የሚገኘው በገዳማት፤ በወንዝ ዳርቻ፤ ገደላማ በሆኑ ተራራዎች፤ በደሰቶች አካባቢ ነው። ዛፎች ለምን ነው የሚቆረጡት? የመኖሪያ ቤት ለመስራት፤ የእርሻ መሬት ለመፍጠር (ምንጠራ) ፤የምግብ ማብሰያ ማገዶ እንጨት (ክሰል)፤ለአጥር ፤ለበረት ሥራ ፤እንዲሁፕ የእርሻና ልዩ ልዩ የእጅ መሳሪያ ለመስራት ነው። ይህ የዛፎች አጠቃቀም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው አሁን በነዚህ 74 ዓመታት ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ። በዋናነት የተቀየረው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በግምት ክ20 ሚሊዮን ወደ 110 ሚሊዮን እየተጠጋ ነው ተብሎ ይገመታል። የሕዝቡ ቁጥር በጨመረ ቁጥር የዛፍ ቆረጣው ከላይ የተጠቀሱቱን ፍⶀጎቶች ለማሟላት በፍጥነት እይቀጠለ በመሄድ ላይ ይገኛል። ዛፎች ለመሆኑ ለምን ይጠቅማሉ? 1) ዛፎች የልዩ ልዩ የተፈጥሮ ጸጋ የሆኑ አእዋስ፤ የወፍ ዘሮች መናሃሪያነት ያገለግላሉ 2) የዛፎች ስር ደግሞ ለም አፈር በነፋስና በዝናብ ተሸርሽሮ እንዳይባክን ይከላከላል 3) ወንዞችና ሀይቆች በአቧራ እንዳይበከሉ ይከላከላሉ 4 ለዝናብ ምንጭ የሆነው የተፈጥሮ የወሀ ተን ከዛፎች ከውቂያኖስ ወደ ደመና ዘልቆ ከቀዘቀዘ በኋላ በዝናብ መልክ ለሚመጣው ሂደት (water cycle) ግብ አት ይሰጣል። ፭) የምግብ (የፍራፍሬ) ምንጭ ፮) የተበከለውን አየር አጽድቶ ለህይወት የሚጠቅም አየር በማበርከት ከዚ ላይ በ4 ቁጥር የሰፈረው ጉዳይ ስፋትና ጥልቀት ያለው ባንድ አገር ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በአህጉር ደረጃ በተያያዘ መልኩ ችግሩ ሊቀረፍ ወይም ሊባባስ የሚችል ነው። በአገር ደረጃ መንግስት ይህን ግንዛቤ አድርጎ የደንን እንክብካቤ በትኩረት በመመልከት ሊያስተካክለው ይገባል። መመሪያ (ፖሊሲ) ሊኖር ይገባል። ከዚህ በታች የምታዩት ፎቶግራፍ የሁለት ተጎራባች አገሮቸን የመሬት መልክዓ ምድር የሚያሳይ ነው። ደርቆ ዛፍ የሌለው (የተራቆተው) ሄይቲ ሲሆን ባብዛኛው ኢትዮጵያን የሚመስል ሲሆን ለምለሙ ደግሞ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ነው። አንደኛው የደን ጥበቃ ፖሊሲ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ግን የለውም። Haiti’s brown landscape contrasts sharply with the rich forests of its neighbor Haiti-Dominican Republic Border, South Of Dajabon, Dominican Republic. Source : An Inconvenient Truth, Al Gore ችግሩ ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ መጠን ፖሊሲውም በርካታ ዘርፎች ያሉት በርካታ መፍተሄዎችን ያዘለ መሆን ይኖርበታል። ዛፍ እንዳይቆረጥ ትዛዝ መስጠት በቂ አይዶለም። አዳዲስ ዛፎች እንዲተከሉ ማድረግ ብቻም አይዶለም። በዋናነት መፍትሄ የሚሆነው ለደን ጥፋት ምክንያት የሆኑትን ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን ምክንያቶች አጥንቶ ለነዚህ አማራጭ መፍትሄ መፈለግ ነው። ፩) ለቤት ሥራ የሚውሉ ልዩ ልዩ ሰው ሰራሽ የሆኑ ቁሳቁስን ገበያ ላይ ማቅረብ (ብረታ ብረት፡ጡብ፡ ፕላስቲክስ፡ፋይበር ግላስ፡ መስታወት፤ሰው ሰራሽ ምርቶችን) ፪) ለአጥር ለበረት ለግንባታ የሚውሉ ተመሳሳይ ሰው ሰራሽ ቁሳቁስን እንደዚሁ ገቢያ ማቅረብ ፫) የእርሻ መሬትን በተመለከተ- በርካታ መፍትሔዎችን መመልከት ያስፈልጋል። ሀ) ተለዋዋጭ ምርቶችን በማምረት መሬቱን ስኬታማ ማድረግ ለ) ማዳበሪያ አጠቃቀምን በእግባቡ አካባቢ በማይበክል መልክ መጠቀም ሐ) ወደ ውጭ አገር ገቢያ ሊቀርቡ የሚችሉ አዳዳስ ምርቶቸን ማምረት መ) በመስኖ የወሀ አቅርቦት በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ ማምረት የመሳሰሉት ሠ) የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ክግብርና በተጨማሪ የተለያዩ ኢንደስትሪን በማቋቋም ማዳበር ማገዶን (ክሰልን) በተመለከተ ቁጥር ሁለትን ይመልክቱ Electricity የመብራት ኋይል ( የኋይል ማመንጫ) ጸሓይ solar energy ነፋስ wind energy ክሰል coal ጋዝ natural gas ማገዶ- ነዳጅ የጸሃይ ሃይል በመጠቀም የእጅ መሳሪያውን በብረትና በፋይበርግላስ ፕላስቲክ በመተካት